Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 12:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ልመካ ብፈልግ አልሞኝም፤ ምክንያቱም የምናገረው እውነት ነው፤ ነገር ግን ማንም ስለ እኔ ከሚያየውና ከሚሰማው ባለፈ የበለጥኩ አድርጎ እንዳያስበኝ ይህን ከመናገር እቆጠባለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መመካት ብፈልግ እንኳ እንደ ሞኝ መቈጠር የለብኝም፤ ምክንያቱም የምናገረው እውነት ነው። ነገር ግን ማንም ስለ እኔ ከሚያየውና ከሚሰማው በላይ እንዳይገምተኝ ከመመካት እቈጠባለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ታዲያ፥ እኔ እውነት ስለምናገር መመካት ብፈልግም ሞኝ አልሆንም፤ ነገር ግን ማንም በእኔ ላይ ከሚያየውና ከእኔ ከሚሰማው በላይ ግምት እንዳይሰጥ ብዬ ከመመካት እቈጠባለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ልመካ ብሻም አላ​ዋቂ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እው​ነ​ቱን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ስላ​ዩ​ኝና ስለ ሰሙኝ እን​ደ​ም​በ​ልጥ አድ​ር​ገው እን​ዳ​ይ​ጠ​ራ​ጠ​ሩኝ ትቸ​ዋ​ለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ልመካ ብወድስ ሞኝ አልሆንም፥ እውነትን እላለሁና፤ ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 12:6
12 Cross References  

እንደገና ይህን እላለሁ፥ ማንም ሰው ሞኝ የሆንሁ አይምሰለው፤ እንደ ሞኝ ለሚያስበኝ፥ እኔም በጥቂቱ እንድመካ እንደ ሞኝ ይቀበለኝ።


በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።


ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እንዳልዋሸሁ ያውቃል።


የዚህን ግልጠት ልዩ ጸባይ በማየት እንዳልታበይ፥ ሥጋዬን መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ።


አእምሮችንን የሳትን ብንሆን፥ የሳትነው ለእግዚአብሔር ነው፤ ጤነኞችም ብንሆን ለእናንተ ነው።


እግዚአብሔር የታመነ የሆነውን ያህል በእርግጥ እኛ ለእናንተ የምንናገረው ቃል “አዎን” እና “አይደለም” አይሆንም።


አጵሎስ እንግዲህ ምንድነው? ጳውሎስስ ምንድነው? በእነርሱ በኩል ያመናችሁ፥ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደሰጣቸው፥ አገልጋዮች ናቸው፤


በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፥ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል፥


እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ነገሬንስ እንደ ከንቱ የሚያደርገው ማን ነው?”


በእርሱ ፊት ስለ እናንተ በተመካሁበት ነገር አላሳፈራችሁኝም፤ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ የተናገርነው እውነት እንደሆነ ሁሉ፥ እንደዚሁም ትምክህታችን በቲቶ ፊት እውነት ሆነ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements