Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ለዚህ ደካሞች መስለን መቅረባችንን በኀፍረት እናገራለሁ። ነገር ግን በሞኝነት እላለሁ፤ ማንም ለመመካት በሚደፍርበት እኔ የምደፍርበት አለኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እኛ ግን ለዚያ እጅግ ደካሞች መሆናችንን እያፈርሁ እናገራለሁ። ማንም በድፍረት በሚመካበት ነገር ሁሉ እኔም ደፍሬ መመካት እንደምችል እንደ ሞኝ እናገራለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የሚያሳፍረኝ ቢሆንም እንኳ እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ብርቱዎች አለመሆናችንን እገልጥላችኋለሁ፤ ነገር ግን ማንም ለመመካት ቢደፍር እኔም እንደ እርሱ ደፍሬ እመካለሁ፤ ይህን የምለው አሁንም እንደ ሞኝ ሆኜ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እኛ እንደ ደካ​ሞች መስ​ለን እንደ ነበ​ርን፥ ይህን በው​ር​ደት እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ነገር ግን ማንም በሚ​ደ​ፍ​ር​በት እኔ ደግሞ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ደካሞች መስለን እንደ ነበርን በውርደት እላለሁ። ነገር ግን በሞኝነት እላለሁ፤ ማንም በሚደፍርበት እኔ ደግሞ እደፍርበታለሁ።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 11:21
8 Cross References  

አንዳንዶች “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ሰውነቱ ሲታይ ግን ደካማ ነው፤ ንግግሩም የተናቀ ነው፤” ይላሉ።


እንደዚህ በመተማመን እየተመካሁ የምናገረው፥ በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አይደለም።


ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኃይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።


በክብርና በውርደት፥ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል። አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤


ሞኝነቴን በጥቂቱ ብትታገሡኝ በወደድኩ ነበር፤ ስለሆነም በእርግጥ ታገሡኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements