2 ቆሮንቶስ 11:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 እንደገና ይህን እላለሁ፥ ማንም ሰው ሞኝ የሆንሁ አይምሰለው፤ እንደ ሞኝ ለሚያስበኝ፥ እኔም በጥቂቱ እንድመካ እንደ ሞኝ ይቀበለኝ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 እንደ ገና ይህን እላለሁ፤ ማንም ሰው እንደ ሞኝ አይቍጠረኝ፤ እናንተም የምትቈጥሩኝ ከሆነ፣ እኔም በጥቂቱ እንድመካ እንደ ሞኝ ተቀበሉኝ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 “ማንም ሰው እኔ ሞኝ የሆንኩ አይምሰለው” ብዬ እንደገና እናገራለሁ። ሞኝ ብመስላችሁም እንኳ ጥቂት እንድመካ እንደ ሞኝ አድርጋችሁ ቊጠሩኝ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ደግሞም እንዲህ እላለሁ፦ ሰነፍ የሚያደርገኝ አይኑር፤ ያውም ብሆን እኔ ጥቂት እመካ ዘንድ እንደ ሰነፍ እንኳ ብሆን ተቀበሉኝ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እንደ ገና እላለሁ፦ ለማንም ሰው ሞኝ የሆንሁ አይምሰለው፤ ያለዚያ ግን እኔ ደግሞ ጥቂት እመካ ዘንድ እንደ ሞኝ እንኳ ሆኜ ተቀበሉኝ። See the chapter |