2 ቆሮንቶስ 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እኛ ግን፥ እግዚአብሔር እንደ ወሰነልን፥ እስከ እናንተ በሚደርስ ወሰን እንጂ፥ ያለ ልክ አንመካም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እኛ ግን ከመጠን በላይ አንመካም፤ የምንመካው እግዚአብሔር በመደበልንና እስከ እናንተም እንኳ በሚደርሰው የአገልግሎታችን ወሰን ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እኛ ግን እስከ እናንተም እንኳ እስክንደርስ እግዚአብሔር በሰጠን የሥራ ክልል እንመካለን እንጂ ከመጠን በላይ የምንመካ አይደለንም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እኛስ ወደ እናንተ እስክንደርስ ድረስ እግዚአብሔር በወሰነልን ሕግና ሥርዐት እንጂ፥ ከዐቅማችን አልፈን እጅግ አንመካም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እኛ ግን እግዚአብሔር እንደ ወሰነልን እስከ እናንተ እንኳ እንደሚደርስ እንደ ክፍላችን ልክ እንጂ ያለ ልክ አንመካም። See the chapter |