2 ዜና መዋዕል 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጽናጽልና በገና መሰንቆም ይዘው በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ መለከት የሚነፉ ካህናት ነበሩ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 መዘምራን የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፣ አሳፍ፣ ኤማን፣ ሄማንና ኤዶታም፣ ወንዶች ልጆቻቸውና የሥጋ ዘመዶቻቸው ሁሉ ያማረ ቀጭን በፍታ ለብሰው፣ ከመሠዊያው በስተምሥራቅ በኩል ቆመው ጸናጽል ይጸነጽሉ፣ በገና ይደረድሩና መሰንቆ ይመቱ ነበር፤ እነርሱም መለከት በሚነፉ አንድ መቶ ሃያ ካህናት ታጅበው ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 መዘምራን የሆኑ ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍ፥ ሄማንና ይዱታን እንዲሁም ወንዶች ልጆቻቸውና ዘመዶቻቸው ሁሉ ጥሩ የበፍታ ልብስ ለብሰው ነበር፤ ሌዋውያኑ ጸናጽልና መሰንቆ በመያዝ በስተ ምሥራቅ በኩል ከመሠዊያው አጠገብ ቆመው ነበር፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ ከአሳፍና ከኤማን፥ ከኤዶትምም ልጆች ጋር ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና ከበሮ፥ መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም ጥሩ በፍታ ለብሰው ጽናጽልና በገና መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር። ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ፥ See the chapter |