2 ዜና መዋዕል 34:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 መሠዊያዎቹንም አፈረሰ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረፁትን ምስሎች አደቀቀ፥ በእስራኤልም አገር ሁሉ የዕጣን መሠዊያዎቹን ሁሉ ቈራረጠ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 መሠዊያዎችንና የአሼራ ምስል ዐምዶችን አፈራረሰ፤ ጣዖታቱን እንደ ዱቄት አደቀቀ፤ በመላው እስራኤል የሚገኙትንም የዕጣን መሠዊያዎች አነካከተ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የሰሜን የእስራኤል ግዛት የነበሩትን የጣዖቶች መሠዊያዎችንና የአሼራ ምስሎችን ሁሉ ሰባበራቸው፤ ጣዖቶቹንም ትቢያ እስኪሆኑ አደቀቃቸው፤ ዕጣን የሚታጠንባቸውንም የጣዖት መሠዊያዎች አንከታክቶ ጣለ፤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 መሠዊያዎቹንም አፈረሰ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረጹትን ምስሎችም አደቀቀ፤ በእስራኤልም ሀገር ሁሉ የኮረብታዎችን መስገጃዎችአጠፋ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 መሥዊያዎቹንም አፈረሰ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረፁትን ምስሎች አደቀቀ፤ በእስራኤልም አገር ሁሉ የፀሐይን ምስሎች ሁሉ ቈራረጠ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ። See the chapter |