Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ዜና መዋዕል 32:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚህም በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር በለኪሶ ሳለ ባርያዎቹን ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስና በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ወደ ይሁዳ ሁሉ እንዲህ ሲል ላከ፦

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚህ በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከሰራዊቱ ሁሉ ጋራ ለኪሶን ከብቦ ሳለ፣ የሚከተለውን መልእክት በጦር መኰንኖቹ አማካይነት፣ ለሕዝቅያስና ከርሱ ጋራ በኢየሩሳሌም ለነበሩት ለይሁዳ ሕዝብ ላከ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህ በኋላ ትንሽ ቈይቶ፥ ንጉሥ ሰናክሬምና ሠራዊቱ ገና በላኪሽ ሳሉ ለሕዝቅያስና ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ለነበሩት ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከዚ​ህም በኋላ የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ጋር በለ​ኪሶ ፊት ሳለ ባሪ​ያ​ዎ​ቹን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ነበሩ ወደ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ እን​ዲህ ሲል ላከ፦

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከዚህም በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር በለኪሶ ፊት ሳለ ባሪያዎቹን ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስና በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ወደ ይሁዳ ሁሉ እንዲህ ሲል ላከ

See the chapter Copy




2 ዜና መዋዕል 32:9
9 Cross References  

ይህ በዚህ እንዳለ የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከላኪሽ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ያም ሠራዊት ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፤


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ፥ ከበቡአትም፥ ወጉአትም።


በላኪሽ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሠረገላውን ከፈረሱ ጋር አያይዢ፤ እርሷ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፤ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።


ራፋስቂስም ተመለሰ፤ የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ስለ ነበር በልብና ከተማ ሲዋጋ አገኘው።


ከዚያ የአሦር ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው። እርሱም በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ላይ ባለችው በላይኛይቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ በቆመ ጊዜ፥


ለኪሶ፥ ቦጽቃት፥ ዔግሎም፥


የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥


“የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ በማን ተማምናችሁ በኢየሩሳሌም ምሽግ ትቀመጣላችሁ?


አዶራይምን፥ ለኪሶን፥ ዓዜቃን፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements