2 ዜና መዋዕል 32:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከተማይቱንም ወርሮ ለመውሰድ፥ በቅጥርም ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌም ሕዝብ ለማስፈራራትና ለማስደንገጥ፥ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኹባቸው ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከዚያም በማስደንገጥና በማስፈራራት ከተማዪቱን ለመያዝ ሲሉ በቅጥሩ ላይ ወደ ተቀመጠው ወደ ኢየሩሳሌም ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በዕብራይስጥ ጮኹ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 የአሦር ባለሥልጣኖች ይህን የዛቻ ቃል በዕብራይስጥ ቋንቋ በቅጽሮቹ ላይ ለነበሩት ለኢየሩሳሌም ሰዎች ከፍ ባለ ድምፅ ያሰሙ ነበር፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት ሕዝቡን አስፈራርተው ተስፋ በማስቈረጥ ከተማይቱን በቀላል ለመያዝ ዐቅደው ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ቅጥሩን እንዲያፈርሱ ከተማዪቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ያስፈራቸውና ያስደነግጣቸው ዘንድ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኽባቸው ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ከተማይቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌም ሕዝብ ያስፈሩና ያስደነግጡ ዘንድ፥ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኹባቸው ነበር። See the chapter |