2 ዜና መዋዕል 31:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በታማኝነትም ቅድስናቸውን ጠብቀዋልና ካህነናቱ በየትውልዳቸው ከሕፃናቶቻቸውና ከሚስቶቻቸው ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው እንዲሁም ከማኅበሩ ሁሉ ጋር ተቈጠሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 በዚህ የትውልድ መዝገብ ላይ የተዘረዘሩትን መላውን የማኅበረ ሰቡን ሕፃናት፣ ሚስቶችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ጨመሯቸው፤ ራሳቸውን በመቀደስ ታማኞች ነበሩና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 እነዚህ ካህናትና ሌዋውያን ራሳቸውን የቀደሱ ታማኞች ስለ ነበሩ የሚመዘገቡት ከሚስቶቻቸው ከልጆቻቸውና በእነርሱ ሥር ከሚተዳደሩት ሰዎች ሁሉ ጋር በአንድነት ነበር፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 በማኅበራቸውም ሁሉ በየትውልዳቸው ለተቈጠሩ ለሚስቶቻቸው፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻቸውም ይሰጡ ነበር፤ በእምነት ፈጽመው ተቀድሰዋልና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 በማኅበሩም ሁሉ በየትውልዳቸው ለተቈጠሩ ለሕፃናቶቻቸውና ለሚስቶቻቸው ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻቸውም ይሰጡ ነበር፤ በእምነት ተቀድሰዋልና። See the chapter |