2 ዜና መዋዕል 30:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 መልእክተኞቹም ከከተማ ወደ ከተማ በኤፍሬምና በምናሴ አገር እስከ ዛብሎን ድረስ ሄዱ፤ በእዚያ ያሉ ሰዎች ግን በንቀት ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 መልእክተኞቹም በኤፍሬምና በምናሴ ምድር ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ በመዘዋወር እስከ ዛብሎን ድረስ ሄዱ፤ ሕዝቡ ግን አንቋሸሻቸው፤ ተሣለቀባቸውም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 መልእክተኞቹ በኤፍሬምና በምናሴ ነገዶች ግዛት ወደሚገኙ ከተማዎች ሁሉ በመሄድ እስከ ዛብሎን ነገድ ሰሜናዊ ግዛት ድረስ ዘለቁ፤ እነዚያ ግን በንቀት እየሳቁ ተሳለቁባቸው፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 መልእክተኞቹም ከከተማ ወደ ከተማ በኤፍሬምና በምናሴ ሀገር እስከ ዛብሎን ሄዱ፤ እነዚያ ግን በንቀት ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 መልእክተኞቹም ከከተማ ወደ ከተማ በኤፍሬምና በምናሴ አገር እስከ ዛብሎን ሄዱ፤ እነዚያ ግን በንቀት ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም። See the chapter |