2 ዜና መዋዕል 28:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፦ “በጌታ ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኃጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የመቅሰፍቱም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነውና።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 “እነዚህን ምርኮኞች እዚህ ማምጣት አልነበረባችሁም፤ አለዚያ እኛ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች እንሆናለን፤ በኀጢአታችንና በበደላችን ላይ ሌላ ልትጨምሩ ታስባላችሁን? በደላችንማ ቀድሞውኑ በዝቷል፤ ቍጣውም በእስራኤል ላይ ነውና” አሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እንዲህም አሉአቸው፦ “እነዚህን እስረኞች ወደዚህ አታምጡብን! ከዚህ ቀደም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን ስላሳዘንን ቊጣው በእኛ ላይ ወርዶአል፤ አሁንም በበደል ላይ በደል እንድንፈጽም ትፈልጋላችሁን?” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 “ደግሞም በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የእግዚአብሔርም የመቅሠፍቱ ቍጣ በእስራኤል ላይ ነውና” አሉአቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ደግሞም “በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኃጢያታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የመቅሰፍቱም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነውና” አሉአቸው። See the chapter |