2 ዜና መዋዕል 27:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ አሸነፋአቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆች በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ተመሳሳ መጠን ያለውን ግብር ገበሩለት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ኢዮአታም የአሞናውያንን ንጉሥ ወግቶ ድል አደረጋቸው። በዚያ ዓመትም አሞናውያን አንድ መቶ መክሊት ጥሬ ብር፣ ዐሥር ሺሕ ቆሮስ ስንዴና ዐሥር ሺሕ ቆሮስ ገብስ ገበሩለት። አሞናውያን በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ይህንኑ ግብር አመጡለት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 በዐሞን ንጉሥና በሠራዊቱ ላይ ጦርነት ከፍቶ ድል አድርጎአቸው ነበር፤ ዐሞናውያንንም በየዓመቱ ለሦስት ዓመት በተከታታይ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚመዝን ብር፥ አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ስንዴና እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ገብስ እንዲገብሩለት አስገደዳቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ፤ አሸነፋቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ ግብር ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆችና ንጉሣቸው በመጀመሪያው፥ በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ሰጡት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ፤ አሸነፋአቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ አሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ አሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆች በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ሰጡት። See the chapter |