Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ዜና መዋዕል 26:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በርና በሸለቆው በር ቅጥሩም በዞረበት ማዕዘን አጠገብ ግንቦችን ሠርቶ መሸጋቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማእዘኑ በር፣ በሸለቆው በርና በቅጥሩ ማእዘን ማማዎች ሠርቶ መሸጋቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዖዝያ በማእዘን ቅጽር በር፥ በሸለቆ ቅጽር በርና በቅጽሩም መጠምዘዣ ላይ መቈጣጠሪያ ግንቦችን በመሥራት የኢየሩሳሌምን ምሽጎች አጠናከረ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዖዝ​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በማ​ዕ​ዘኑ በርና በሸ​ለ​ቆው በር፥ ቅጥ​ሩም በዞ​ረ​በት ማዕ​ዘን አጠ​ገብ ግን​ቦ​ችን ሠርቶ መሸ​ጋ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በርና በሸለቆው በር ቅጥሩም በዞረበት ማዕዘን አጠገብ ግንቦችን ሠርቶ መሸጋቸው።

See the chapter Copy




2 ዜና መዋዕል 26:9
10 Cross References  

ሐኑንና የዛኖሐ ሰዎችም “የሸለቆ በር” አደሱ፤ መልሰው ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጁ፤ ደግሞም እስከ “የፍግ በር” ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።


የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን በቤት-ሳሚስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር ከኤፍሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈረሰ።


ዮአስም የአካዝያስን ልጅ፥ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ለመድረስ ገሠገሠ፤ እዚያም እንደ ደረሰ ከኤፍሬም ቅጽር በር “የማእዘን ቅጽር በር” ተብሎ እስከሚጠራው በር ድረስ ጠቅላላ ርዝመቱ ሁለት መቶ ሜትር የሆነውን የቅጽር ግንብ አፈረሰ።


ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ፥ እንደ ዓረባ ትሆናለች፤ እርሷም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው የበሯ ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።


“ከሐናንኤል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ ለጌታ ከተማ የሚሠራበት ዘመን፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


ከማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ጀምረው እስከ “የበግ በር” ድረስ ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎች አደሱ።


ከእርሱም በኋላ የሔናዳድ ልጅ ቢኑይ ከዓዛርያ ቤት ጀምሮ እስከ የግንቡ መደገፊያ ድረስ ሌላውን ክፍል አደሰ።


በሌሊት በፈፋው በኩል ወጥቼ ቅጥሩን ተመለከትኩ፤ ተመልሼም በሸለቆው በር ገባሁ፥ ከዚያም ተመለስኩ።


በሌሊትም በሸለቆው በር ወጣሁ፥ ወደ “የዘንዶ ምንጭ” እና ወደ “የፍግ በር” ሄድኩ፤ የፈረሰውን የኢየሩሳሌምን ቅጥርና በእሳት የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትኩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements