2 ዜና መዋዕል 24:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 የሶርያውያንም ሠራዊት ቍጥር ጥቂት ሆኖ ሳለ ጌታ ታላቅን ሠራዊት አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ ይህም የሆነው የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ትተው ስለ ነበረ ነው። እነርሱም በኢዮአስ ላይ ፍርድ ፈረዱበት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 የሶርያ ሰራዊት ሰዎች ጥቂት ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር በጣም የሚበልጠውን ሰራዊት በእጃቸው አሳልፎ ሰጠ፤ ይሁዳ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለ ተወ፣ በኢዮአስ ላይ ተፈረደበት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 የሶርያ ሠራዊት ቊጥር ጥቂት ነበር፤ ነገር ግን እጅግ ብዙ የሆነውን የይሁዳን ሠራዊት ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ይህም የሆነው እነርሱ የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ስለ ተዉ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢዮአስ ላይ ትክክለኛ ፍርድ ተፈጸመበት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 የሶርያውያንም ሠራዊት ቍጥር ጥቂት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ብዙውንና ጠንካራውን ሠራዊት አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ዘንግተዋልና። በኢዮአስም ላይ ፈረደበት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 የሶርያውያንም ሠራዊት ቍጥር ጥቂት ሆኖ ሳለ እግዚአብሔር ታላቅን ሠራዊት አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ ይህም የሆነው የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ስለ ነበረ ነው። እነርሱም በኢዮአስ ላይ ፍርድ ፈረዱበት። See the chapter |