2 ዜና መዋዕል 22:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አካዝያስንም ፈልገው፥ በሰማርያም ተሸሽጎ ሳለ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት እንዲህም ብለው ቀበሩት፦ “በፍጹም ልብ ጌታን የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው።” ከአካዝያስም ቤት ማንም መንግሥቱን ለመግዛት የሚችል አልነበረም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ከዚያም አካዝያስን ለመፈለግ ሄደ፤ የእርሱም ሰዎች አካዝያስን በሰማርያ ከተደበቀበት አግኝተው ያዙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት። “እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው” በማለት ቀበሩት። ስለዚህ ከአካዝያስ ቤት የመንግሥቱን ሥልጣን ይይዝ ዘንድ የሚችል ሰው አልነበረም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አካዝያስንም ፈልገው በሰማርያ ተሸሽጎ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት፤ ነገር ግን የተቻለውን ያኽል እግዚአብሔርን ያገለግል ስለ ነበረው ስለ አያቱ ስለ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ክብር ሲሉ ሬሳውን ቀበሩት። ከአካዝያስ ቤተሰብ አባላት መካከል መንግሥቱን ሊመራ የሚችል አንድም ሰው አልተረፈም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አካዝያስንም ፈለገው፤ በሰማርያም እየታከመ ሳለ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አመጡት፤ እርሱም ገደለው፦ እነርሱም፥ “በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበሩት። ከአካዝያስም ቤት ማንም መንግሥትን ይይዝ ዘንድ የሚችል አልነበረም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አካዝያስንም ፈልገው፤ በሰማርያም ተሸሽጎ ሳለ አገኙት፤ ወደኢዩም አምጥተው ገደሉትና “በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን የፈለገው የኢዮሳፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበሩት። ከአካዝያስም ቤት ማንም መንግሥትን ይይዝ ዘንድ የሚችል አልነበረም። See the chapter |