2 ዜና መዋዕል 21:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ኢዮራምም ከአለቆቹና ከሰረገሎቹ ሁሉ ጋር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነሥቶ እርሱንና የሰረገሎቹን አለቆች ከብበው የነበሩትን የኤዶምያስን ሰዎች መታ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ስለዚህ ኢዮራም የጦር ሹማምቱና ሠረገላዎቹን ሁሉ አሰልፎ ተሻገረ። በሌሊትም ተነሥቶ እርሱንና የሠረገላ አዛዦቹን ሁሉ የከበቧቸውን ኤዶማውያንን መታ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ስለዚህ ኢዮራም የጦር መኰንኖቹንና ሠረገሎቹን ይዞ በመዝመት ኤዶምን ወረረ፤ በዚያም የኤዶም ሠራዊት እነርሱን ከበባቸው፤ ነገር ግን ኢዮራምና ሠራዊቱ በሌሊት ከበባውን ጥሰው ለማምለጥ ቻሉ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ኢዮራምም ከአለቆቹና ከሰረገሎቹ ሁሉ ጋር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነሥቶ እርሱንና የሰረገሎቹን አለቆች ከብበው የነበሩትን የኤዶምያስ ሰዎችን መታ፤ ሕዝቡም ወደ ድንኳናቸው ሸሹ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ኢዮራምም ከአለቆቹና ከሰረገሎቹ ሁሉ ጋር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነሥቶ እርሱንና የሰረገሎቹን አለቆች ከብበው የነበሩትን የኤዶምያስን ሰዎች መታ። See the chapter |