2 ዜና መዋዕል 20:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ‘ክፉ ነገር፥ ሰይፍ ወይም ፍርድ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።’ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ‘የፍርድ ሰይፍም ሆነ የቸነፈር ወይም የራብ መከራ ቢደርስብን፣ ስምህ በተጠራበት በዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት፣ በፊትህ ቆመን በጭንቀታችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ትሰማናለህ፤ ታድነናለህም።’ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ‘እኛን ለመቅጣት ጦርነትን፥ ቸነፈርን ወይም ራብን የመሳሰለውን መቅሠፍት ብታደርስብን የአንተ ስም ወደሚጠራበት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት መጥተን በመቆም ከመከራችን እንድታድነን ወደ አንተ እንጸልያለን፤ አንተም ጸሎታችንን ሰምተህ በመታደግ ታድነናለህ’ ብሎ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እንዲህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆማለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመከራችንም ወደ አንተ እንጮኻለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ‘ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ’ አሉ። See the chapter |