2 ዜና መዋዕል 2:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ሰሎሞንም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ሁሉ አባቱ ዳዊት እንደ ቈጠራቸው ቈጠረ፤ መቶ ኀምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ተገኙ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ሰሎሞን አባቱ ዳዊት ካደረገው ቈጠራ በኋላ፣ በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ሁሉ ቈጠረ፤ ቍጥራቸውም አንድ መቶ ዐምሳ ሦስት ሺሕ ስድስት መቶ ሆነ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ንጉሥ ሰሎሞን ከዚህ በፊት አባቱ ዳዊት ባደረገው ዐይነት በእስራኤል ምድር የሚኖሩትን የውጪ አገር ሰዎች ቈጠረ፤ በዚህም ዐይነት በግዛቱ ውስጥ አንድ መቶ ኀምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ መጻተኞች መኖራቸው ተረጋገጠ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ሰሎሞንም አባቱ ዳዊት ከቈጠራቸው ጋር ያልተቈጠሩ በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ሁሉ ሰበሰበ፤ ቍጠራቸውም መቶ ኀምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሆኖ ተገኘ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ሰሎሞንም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ሁሉ አባቱ ዳዊት እንደ ቈጠራቸው ቈጠረ፤ መቶ አምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ተገኙ። See the chapter |