Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ዜና መዋዕል 2:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የጢሮስ ንጉሥም ኪራም ለሰሎሞን በላከው ደብዳቤ እንዲህ ብሎ መለስ ሰጠ፦ “ጌታ ሕዝቡን ወድዶአልና በእነርሱ ላይ አነገሠህ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራምም ለሰሎሞን እንዲህ ሲል በደብዳቤ መለሰለት፤ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወድድ አንተን በእነርሱ ላይ አነገሠህ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ንጉሥ ኪራምም ለንጉሥ ሰሎሞን በደብዳቤ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወድ አንተ በእነርሱ ላይ እንድትነግሥ አደረገ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራ​ምም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወድ​ዶ​አ​ልና በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ” ሲል ለሰ​ሎ​ሞን ጻፈ​ለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራምም “እግዚአብሔር ሕዝቡን ወድዶአልና በላያቸው አነገሠህ፤” ብሎ ለሰሎሞን መልእክት ላከ።

See the chapter Copy




2 ዜና መዋዕል 2:11
6 Cross References  

በአምላክህ በጌታ ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ላይ ሊያስቀምጥህ የወደደህ አምላክህ ጌታ ብሩክ ይሁን፤ አምላክህ እስራኤልን ለዘለዓለም ሊያጸናቸው ወድዶአቸዋልና ስለዚህ ፍርድና ጽድቅ እንድታደርግ በእነርሱ ላይ አነገሠህ።”


ጌታ አምላክህ ይመስገን! እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘላለማዊ ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል።”


ስሙ ለዘለዓለም ይታወስ፥ እንደ ፀሐይ ዕድሜ ስሙ ጸንቶ ይኑር፥ የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሱ ይባረኩ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑት፥


በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።


ሕዝባችንን ይወዳልና፤ ምኵራብም የሠራልን እርሱ ነው።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements