2 ዜና መዋዕል 18:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የክንዓና ልጅ ሰዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ሶሪያውያንን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’ ” አለ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በዚህ ጊዜ፣ የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሶርያውያን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’ ” አለ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ከእነርሱም አንዱ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ከብረት ቀንዶችን ሠርቶ አክዓብን “እግዚአብሔር ‘በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ይልሃል” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 የካህናን ልጅ ሴዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በእነዚህ ትወጋለህ” አለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 የክንዓና ልጅ ሰዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ሶሪያውያንን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋለህ’” አለ። See the chapter |