2 ዜና መዋዕል 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በየጥዋቱና በየማታውም ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መዓዛው ያማረ ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የተቀደሰውንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የጌታን ትእዛዝ እንጠብቃለን፥ እናንተ ግን ትታችሁታል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እነርሱም በየጧቱና በየማታው የሚቃጠል መሥዋዕትና ሽታው ደስ የሚያሰኝ ዕጣን ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ፤ የገጹን ኅብስት በሥርዐቱ መሠረት በነጻው ጠረጴዛ ላይ ያኖራሉ፤ በየማታውም በወርቁ መቅረዝ ላይ ያሉትን ቀንዲሎች ያበራሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንፈጽማለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 በየቀኑ ጧትና ማታ መዓዛው ጣፋጭ የሆነውን ዕጣንና የሚቃጠለውን የእንስሳት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያሳርጋሉ፤ በነጻው ገበታም ላይ የመባ ኅብስት ያቀርባሉ፤ ዘወትር ማታ ማታም ከወርቅ በተሠራው መቅረዝ ላይ ያሉትን ቀንዲሎች ያበራሉ፤ እኛ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንፈጽማለን፤ እናንተ ግን እግዚአብሔርን ትታችኋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹን ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል። See the chapter |