2 ዜና መዋዕል 13:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ለእኛ ግን አምላካችን ጌታ ነው፥ አልተውነውም፤ የጌታም አገልጋዮች የአሮን ልጆች ካህናቱ ሌዋውያኑም በሥራቸው ከእኛ ጋር ናቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 “ለእኛ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱንም አልተውንም፤ እግዚአብሔርን በማገልገል ላይ ያሉት ካህናት የአሮን ልጆች ሲሆኑ፣ ረዳቶቻቸውም ሌዋውያኑ ናቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 “እኛ ግን አሁንም እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ከእርሱም ፈቀቅ አላልንም፤ የአሮን ልጆች የሆኑ ካህናትም እግዚአብሔርን ማገልገላቸውን አላቋረጡም፤ ሌዋውያንም እንደ ወትሮው ሁሉ ካህናትን ይረዳሉ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እኛ ግን አምላካችን እግዚአብሔርን አልተውነውም፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች የአሮን ልጆች ካህናቱና ሌዋውያኑ በየሰሞናቸው ያገለግሉታል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ለእኛ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤ አልተውነውም፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች የአሮን ልጆች ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም በሥራቸው ከእኛ ጋር ናቸው። See the chapter |