2 ዜና መዋዕል 10:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልን’ ለሚሉኝ ሕዝብ እንድመልስላቸው የምትመክሩኝ ምንድነው?” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እንዲህም አላቸው፤ “ ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች የምትሰጡኝ ምክር ምንድን ነው? ምንስ ብለን እንመልስላቸው?” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 “ላደርገው ስለሚገባኝ ነገር ምን ትመክሩኛላችሁ? የአገዛዝ ቀንበር እንዳቀልላቸው ለጠየቁኝስ ሰዎች ምን መልስ ልስጣቸው?” ሲል ጠየቃቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እርሱም፥ “አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድን ነው?” አላቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እርሱም “‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልን’ ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው?” አላቸው። See the chapter |