Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ዜና መዋዕል 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሰሎሞንም በጌታ ፊት በመገናኛው ድንኳን አጠገብ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጣ፥ በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጥቶ በላዩ ላይ አንድ ሺሕ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ንጉሡም እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን ፊት ለፊት ባለው ከነሐስ በተሠራው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት በማቅረብ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ አንድ ሺህ እንስሶችንም አሳርዶ በመሠዊያው ላይ እንዲቃጠሉ አደረገ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ን​ኳኑ አጠ​ገብ ወዳ​ለው ወደ ናሱ መሠ​ዊያ ወጣ፤ በዚ​ያም አንድ ሺህ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን አጠገብ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጣ፤ በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።

See the chapter Copy




2 ዜና መዋዕል 1:6
6 Cross References  

ታላቁ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለ ነበር አንድ ቀን ሰሎሞን መሥዋዕትን ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ፤ ከዚህም በፊት በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቅርቧል።


በማግስቱም ለጌታ መሥዋዕት ሰዉ፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለጌታ አቀረቡ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቁርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።


ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።


ሊባኖስ ለማንደጃ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም።


ንጉሥ ሰሎሞንና በፊቱ የተሰበሰበው መላው የእስራኤል ሕዝብ፥ ከእርሱ ጋር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ሆነው፥ ከብዛቱም የተነሣ የማይቆጠር ብዙ በግና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ ነበር።


በዚያን ጊዜም ሰሎሞን በወለሉ ፊት በሠራው በጌታ መሠዊያ ላይ ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements