Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ዜና መዋዕል 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር ጉባኤው ሁሉ የጌታ ባርያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው መገናኛ ድንኳን በዚያ ነበረና በገባዖን ወዳለው ወደ ኮረብታማው ስፍራ ሄዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የአምላክ የመገናኛ ድንኳን በዚያ ስለ ነበር፣ ሰሎሞንና መላው ጉባኤ በገባዖን ወዳለው ኰረብታ ሄዱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በገባዖን ወደሚገኘው ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራ አብረውት እንዲሄዱ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወደዚያ የሄዱበትም ምክንያት፥ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው፥ እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በዚያው በገባዖን ስለሚገኝ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ በም​ድረ በዳ የሠ​ራው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ክር ድን​ኳን በዚያ ነበ​ረና በገ​ባ​ዖን ወዳ​ለው የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ሄዱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር ጉባኤው ሁሉ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን በዚያ ነበረና በገባዖን ወዳለው የኮረብታው መስገጃ ሄዱ።

See the chapter Copy




2 ዜና መዋዕል 1:3
12 Cross References  

ሙሴም በምድረ በዳ የሠራት የጌታ ማደሪያና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያ በዚያን ጊዜ በገባዖን ባለው በኮረብታው መስገጃ ነበሩ።


ካህኑን ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በጌታ ማደሪያ ፊት እንዲያገለግሉ በዚያ ተዋቸው፤


የጌታ ባርያም ሙሴ እንደ ጌታ ቃል በሞዓብ ምድር ሞተ።


ጌታም ሙሴን ጠርቶ ከመገናኛው ድንኳን እንዲህ ሲል ተናገረው፦


ከዚህ በኋላ ደመናው የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፥ የጌታም ክብር ማደሪያውን ሞላ።


“በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ማደሪያ ትተክላለህ።


ሥራ ሲሠሩ ከነበሩት ጥበበኞች የሆኑት ሁሉ ማደሪያውን ሠሩ፤ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ፥ ኪሩቤልም የተጠለፈባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ሠሩ።


የጌታን ታቦት፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ እንዲሁም በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ፥ ሌዋውያንና ካህናት አመጡ።


ሰሎሞንም በገባዖን ካለው ከኮረብታው ስፍራ ከመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ።


የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements