Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ጢሞቴዎስ 5:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጽ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሌሎች አይተው እንዲጠነቀቁ ኀጢአት የሚሠሩትን በጉባኤ ፊት ገሥጻቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሌሎች እንዲፈሩ ኃጢአት የሚሠሩትን በሰዎች ሁሉ ፊት ገሥጽ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኀጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሰሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው።

See the chapter Copy




1 ጢሞቴዎስ 5:20
15 Cross References  

ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ተግተህ ሥራ፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።


ይህ ምስክርነት እውነት ነው። በዚህም ምክንያት እነርሱን አጥብቀህ ገሥጽ፤ ይህን የምታደርገው በእምነት ረገድ እንዲጸኑና


በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህንም በሰሙ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።


ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም በማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አይደረግም።”


ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ከእነዚህ መካከል ናቸው፤ እነርሱም እንዳይሳደቡ ለማስተማር ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቻቸዋለሁ።


ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ፤ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።


ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።


የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከልህ ከቶ አይደገምም።


ሕዝቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈራል፥ ከዚያም ወዲያ አይዳፈርም።


ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፤ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፤ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤


“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ በጽኑ ገሥጸው።


እነሆ፥ ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ለእንዴት ዓይነት ትጋት፥ ለእንዴት ዓይነት ራስን የማንጻት ጉጉት፥ ለእንዴት ዓይነት ቊጣ፥ ለእንዴት ዓይነት ፍርሃት፥ ለእንዴት ዓይነት ናፍቆት፥ ለእንዴት ዓይነት ቅንዓት፥ ለእንዴት ዓይነት ቅጣት እንዳደረሳችሁ ተመልከቱ! በዚህም ጉዳይ ንጹሓን መሆናችሁን በሁሉ ረገድ አስመስክራችኋል።


ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፤ ይልቁን ግለጡት፤


ይህንንም በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements