1 ጢሞቴዎስ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እነርሱም መጋባትን ይከለክላሉ፤ አምነውም እውነትን ላወቁት፥ ከምስጋና ጋር እግዚአብሔር የፈጠረውን ምግብ ከመቀበል እንዲቆጠቡ ያዝዛሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እነርሱ፣ ሰዎች እንዳያገቡ ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎች እግዚአብሔር የፈጠረውን፣ በምስጋናም የሚቀበሉትን እንዳይበሉ ያዝዛሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እንደእነዚህ ያሉት ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎችም እርሱን እያመሰገኑ እንዲመገቡት እግዚአብሔር የፈጠረላቸውን ምግብ “አትብሉ” እያሉ ይከለክላሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፤ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፥ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ። See the chapter |