1 ጢሞቴዎስ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ለዚህም እንደክማለን እንታገላለንም፤ ምክንያቱም ሰውን ሁሉ በተለይም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስላደረግን ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ለዚህ ብለን እንጥራለን፤ እንደክማለንም፤ ይኸውም ለሰዎች ሁሉ፣ በተለይም ለሚያምኑት አዳኝ በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ተስፋ ስለምናደርግ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እኛ ሰዎችን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን ሁሉ በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ የምናደርግ ስለ ሆነ በሥራ እንደክማለን፤ እንታገላለን። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፤ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው። See the chapter |