Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ነገር ግን፥ “የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” ማለታቸው ሳሙኤልን አላስደሰተውም፤ ስለዚህ ወደ ጌታ ጸለየ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ነገር ግን፣ “የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” ማለታቸው ሳሙኤልን አላስደሰተውም፤ ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ንጉሥ ያነግሥላቸው ዘንድ በመጠየቃቸውም ሳሙኤል አዝኖ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “የሚ​ፈ​ር​ድ​ልን ንጉሥ ስጠን” ባሉት ጊዜም ነገሩ ሳሙ​ኤ​ልን አስ​ከ​ፋው፤ ሳሙ​ኤ​ልም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሚፈርድልንም ንጉሥ ስጠን ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን አስከፋው፥ ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 8:6
18 Cross References  

“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።


ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ ጌታ እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በጌታ ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ።”


በፍቅሬ ፋንታ ከሰሱኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።


ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “ጥናህን ውሰድ፥ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፥ ዕጣንም ጨምርበት፥ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው አስተስርይላቸውም፤ ከጌታ ዘንድ ቁጣ ወጥቶአልና መቅሠፍት ጀምሮአል።”


እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው በመስገድ እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ! አንተ የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን?”


ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ ጌታንም እንዲህ አለው፦ “ወደ ቁርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”


አሁንም ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው፥ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ” አለ።


ሙሴም አሮንን፦ “ይህንን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ?” አለው።


በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በምንም ዓይነት ነገር አትጨነቁ።


ከዚያ በኋላ ሳሙኤል፥ “እስራኤልን ሁሉ በምጽጳ ሰብስቡ፤ እኔም ስለ እናንተ ወደ ጌታ እጸልያለሁ” አለ።


ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ፤ ‘የለም፤ ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ። ስለዚህ በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ሆናችሁ በጌታ ፊት ቅረቡ።”


የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ ግን፥ አምላካችሁ ጌታ ንጉሣችሁ ቢሆንም እንኳን፥ ‘አይሆንም፤ የሚገዛን ንጉሥ እንፈልጋለን’ አላችሁ።


በየከተማህ ሁሉ እንዲያድንህ ንጉሥህ ወዴት አለ? ስለ እነርሱም፦ “ንጉሥንና አለቆችን ስጠኝ” ብለህ የተናገርኸው መሳፍንቶችህ ወዴት አሉ?


ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፥ “ሌላው በደላችን ሳያንስ፥ ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ክፋት ስላደረግን እንዳንሞት፥ ለአገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ጸልይልን” አሉት።


ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት ጌታን እንዳልበድል ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements