Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎችም ይህን ተመልክተው፥ በዚያው ዕለት ወደ ዔቅሮን ተመለሱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦችም ይህን ሁሉ ካዩ በኋላ በዚያ ዕለት ወደ አቃሮን ተመለሱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አምስቱም የፍልስጥኤም ገዢዎች ይህን ሁሉ ሲመለከቱ ቈይተው በዚያው ቀን ወደ ዔቅሮን ተመለሱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነ​ዚ​ያም የፍ​ልስጥኤ​ማ​ው​ያን አም​ስቱ አለ​ቆች አይ​ተው በዚ​ያው ቀን ወደ አስ​ቀ​ሎና ተመ​ለሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ፍልስጥኤማውያንም አምስቱ አለቆች ባዩት ጊዜ በዚያው ቀን ወደ አስቀሎና ተመለሱ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 6:16
7 Cross References  

እነርሱም፥ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዓይነት በመሆኑ፥ በፍልስጥኤማውያን ገዥዎች ቍጥር አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ።


እነዚህም አሕዛብ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማትስ መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ።


በግብጽ ፊት ለፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል እስካለችው የከነዓናውያን ሆና እስከ ተቈጠረችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን፥ የአስቀሎና፥ የጌት፥ የአቃሮን፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ናቸው፥ የኤዋውያን የሆኑትም እንዲሁ፥


ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን በመያዝ፥ እምቧ እያሉ፥ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሼሜሽ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ተከተሏቸው።


ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ዔቅሮን ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት ዔቅሮን በገባ ጊዜም፥ የዔቅሮን ሕዝብ፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ያመጡብን እኛንና ሕዝባችንን ለማስፈጀት ነው” በማለት ጮኹ።


የፍልስጥኤማውያን ገዦች ወደ እርሷ ሄደው፥ “እርሱን አስረን በቊጥጥራችን ሥር በማዋል ልናሸንፈው እንዴት እንደምንችልና የብርታቱ ታላቅነት ምስጢር ምን እንደሆነ እንዲያሳይሽ እስቲ አባብይው፤ ይህን ካደረግሽ እያንዳንዳችን አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ጥሬ ብር እንሰጥሻለን” አሏት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements