Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 4:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ፍልስጥኤማውያንም ፈርተው እንዲህ አሉ፤ “አምላክ ወደ ሰፈሩ መጥቷል፤ ወዮልን! ከዚህ አስቀድሞ እንዲህ ዓይነት ነገር አጋጥሞን አያውቅም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ፍልስጥኤማውያንም ፈርተው እንዲህ አሉ፤ “አምላክ ወደ ሰፈሩ መጥቷል፤ ወዮልን! እንዲህ ዐይነት ነገር ገጥሞን አያውቅም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ፈርተው እንዲህ አሉ፦ “ከአማልክት አንዱ ወደ እነርሱ ሰፈር መጥቶአል፤ እንግዲህ ወዮልን! ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ሁኔታ ደርሶብን አያውቅም፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ፈር​ተው፥ “አማ​ል​ክት ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰፈር መጥ​ተ​ዋል” አሉ። ደግ​ሞም እን​ዲህ አሉ፥ “ወዮ​ልን! አቤቱ፥ ዛሬ አድ​ነን፤ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ እን​ዲህ ያለ ነገር አል​ሆ​ነ​ምና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ፍልስጥኤማውያንም ፈርተው፥ እግዚአብሔር ወደ ሰፈር መጥቶአል አሉ። ደግሞም እንዲህ አሉ፦ ወዮልን፥ ከዚህ አስቀድሞ እንዲህ ያለ ነገር አልሆነም።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 4:7
6 Cross References  

እርሱ አንባቸው ካልሸጣቸው፥ ጌታም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ እንዴት አንዱ ሺህን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺህ ያባርራሉ?


የሰረገሎቹንም ጎማ አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አስገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “ጌታ ግብፃውያንን ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።


ፍልስጥኤማውያንም ይህን ታላቅ የሆታ ድምፅ ሲሰሙ፥ “በዕብራውያን ሰፈር የምንሰማው ይህ ሁሉ የሆታ ድምፅ ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁ። የጌታም ታቦት ወደ ሰፈር መምጣቱን በተረዱ ጊዜ፤


ወዮልን! ከእነዚህ ኀያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? ግብፃውያንን በምድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅሠፍት የመቱ እነዚሁ አማልክት ናቸው፤


ጌታ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements