Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 31:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያም የሳኦልን ራስ ቆርጠው፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈው፥ የምሥራቹን በየቤተ ጣዖቶቻቸውና በሕዝባቸው መካከል እንዲናገሩ ወደ ፍልስጥኤም ምድር ሁሉ መልክተኞች ላኩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም የሳኦልን ራስ ቈርጠው፣ የጦር መሣሪያውንም ገፍፈው፣ ለቤተ ጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲናገሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክተኞችን ላኩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የሳኦልንም ራስ ቈርጠው የጦር ልብሱንም ገፈው በማስያዝ ለአማልክቶቻቸው መቅደስና ለሕዝባቸው የድሉን ዜና ያበሥሩ ዘንድ መልእክተኞቻቸውን ላኩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አገ​ላ​ብ​ጠ​ውም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ገፈፉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ላሉ ለጣ​ዖ​ታ​ቱና ለሕ​ዝቡ የም​ሥ​ራች ይነ​ግሩ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሁሉ ላኩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የሳኦልንም ራስ ቈርጠው የጦር ዕቃውን ገፍፈው ለጣዖታቱ መቅደስ ለሕዝቡም የምስራች ይሰጥ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ሁሉ ሰደዱ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 31:9
7 Cross References  

የፍልስጥኤም ቆነጃጅት ደስ እንዳይላቸው፤ ያልተገረዙት ሴት ልጆች እልል እንዳይሉ፤ ይህን በጌት አትናገሩ፤ በአስቀሎናም መንገዶች አታውጁ፤


ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥ “እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝ፥ እንዳያዋርዱኝም፥ አንተው ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፥ እምቢ አለው። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት።


ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የጦር መሣሪያዎቹን ግን በራሱ ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ።


ዳዊት ሮጦ በላዩ ላይ ቆመ፤ ከዚያም የፍልስጥኤማዊውን ሰይፍ ከሰገባው መዞ አወጣው፤ እርሱንም ከገደለው በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ።


በማግስቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ለመግፈፍ ሲመጡ፥ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገቿቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements