1 ሳሙኤል 30:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ከዳዊት ተከታዮች ክፉዎቹና ምግባረ ቢሶቹ ግን፥ “አብረውን ስላልዘመቱ ካመጣነው ምርኮ አናካፍላቸውም፤ እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ብቻ ይዞ መሄድ ይችላል” አሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ከዳዊት ተከታዮች ክፉዎቹና ምናምንቴዎቹ ሁሉ ግን፣ “ዐብረውን ስላልዘመቱ ካመጣነው ምርኮ አናካፍላቸውም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ መሄድ ይችላል” አሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ነገር ግን ከዳዊት ጋር አብረው ከሄዱት መካከል የብልግና ጠባይ ያለባቸው አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች “ከእኛ ጋር ወደ ጦርነቱ ስላልሄዱ ምርኮ ልናካፍላቸው አይገባም፤ ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ብቻ ተረክበው ወዲያ ይሂዱ” አሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ከዳዊትም ጋር ከሄዱ ሰዎች ክፉዎቹና ዐመፀኞቹ ሁሉ፥ “እነዚህ ከእኛ ጋር አልመጡምና እየራሳቸው ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካስጣልነው ምርኮ ምንም አንሰጣቸውም” አሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ከዳዊትም ጋር ከሄዱ ሰዎች ክፋዎቹና ምናምንቴዎቹ ሁሉ፦ እነዚህ ከእኛ ጋር አልመጡምና እየራሳቸው ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካስጣልነው ምርኮ ምንም አንሰጣቸውም አሉ። See the chapter |