Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 30:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሁለት መቶዎቹ እጅግ ዝለው ስለ ነበር ወንዙን መሻገር አልቻሉም። ነገር ግን ዳዊትና አራት መቶ ሰዎች መከታተላቸውን ቀጠሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሁለት መቶዎቹ እጅግ ዝለው ስለ ነበር ወንዙን መሻገር አልቻሉምና። ነገር ግን ዳዊትና አራት መቶ ሰዎች መከታተላቸውን ቀጠሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዳዊት ግን ከአራት መቶ ተከታዮቹ ጋር ማሳደዱን ቀጠለ፤ ሌሎቹ ሁለት መቶ ተከታዮቹ ግን ወንዙን ለመሻገር ስለ ደከሙ ወደ ኋላ ቀሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳ​ደዱ፤ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦ​ሦር ወን​ዝን መሻ​ገር ደክ​መ​ዋ​ልና በኋላ ቀሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ዳዊትም ከእርሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳደዱ፥ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦሦር ወንዝን መሻገር ደክመዋልና በኋላ ቀሩ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 30:10
7 Cross References  

ከዚያም ዳዊት እጅግ በመድከማቸው ምክንያት ሊከተሉት ወዳልቻሉት በብሦር ወንዝ ቀርተው ወደነበሩት ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነርሱም ዳዊትንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ለመቀበል ወጡ። ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እነርሱ እንደ ቀረቡም ዳዊት ሰላምታ ሰጣቸው።


ስለዚህ ዳዊትና አብረውት የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ብሦር ተብሎ ከሚጠራው ወንዝ ሲደርሱ፤ ጥቂቶቹ በብሦር ወንዝ ቆዩ።


በዚያች ዕለት ፍልስጥኤማውያንን ከሚክማስ እስከ አያሎን ድረስ ከመቷቸው በኋላ ሕዝቡ እጅግ ዝለው ነበር።


ከዚያም ሳኦልና ሰዎቹ ተሰብስበው ወደ ውጊያው ሄዱ። እዚያም ፍልስጥኤማውያን ግራ በመጋባት በታላቅ ትርምስ እርስ በርሳቸው በሰይፍ ይጋደሉ ነበር።


እነርሱም በምድረ በዳ አንድ ግብፃዊ አገኙ፤ ወደ ዳዊትም አመጡት። የሚጠጣውን ውሃና የሚበላውን ምግብ ሰጡት።


ብላቴኖች ይደክማሉ፥ ይታክታሉም፤ ጐበዛትም ፈጽሞ ይወድቃሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements