1 ሳሙኤል 28:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እርሱም፥ “መልኩ ምን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርሷም፥ “ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየወጣ ነው” አለችው። ሳኦልም ሴትዮዋ ያየችው ሳሙኤል መሆኑን ዐወቀ፤ በመሬትም ላይ ተደፍቶ እጅ ነሣ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እርሱም፣ “ምን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርሷም፣ “ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየወጣ ነው” አለችው። ሳኦልም ሴትዮዋ ያየችው ሳሙኤል መሆኑን ዐወቀ፤ በመሬትም ላይ ተደፍቶ እጅ ነሣ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እርሱም “መልኩ ምንን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እነሆ፥ ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየተነሣ ነው” ስትል መለሰችለት። ሳኦልም ያ ሳሙኤል መሆኑን ዐውቆ ስለ ክብሩ በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እርሱም፥ “ምን አየሽ?” አላት። እርስዋም፥ “ቀጥ ያለ ሽማግሌ ሰው ከምድር ወጣ፤ መጐናጸፊያም ተጐናጽፎአል” አለች። ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ሆነ ዐወቀ፤ በፊቱም ወደ ምድር ጐንበስ ብሎ ሰገደለት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እርሱም፦ መልኩ ምን ዓይነት ነው? አላት። እርስዋም፦ ሽማግሌ ሰው ወጣ፥ መጎናጸፊያም ተጎናጽፎአል አለች። ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ሆነ አወቀ፥ በፊቱም ተጎነበሰ፥ በምድርም ላይ እጅ ነሣ። See the chapter |