Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 26:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ዳዊት ግን አቢሳን እንዲህ አለው፤ “አትግደለው! ጌታ በቀባው ላይ እጁን አንሥቶ ከበደል ነጻ የሚሆን ማን ነው?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ዳዊት ግን አቢሳን እንዲህ አለው፤ “አትግደለው! እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን አንሥቶ ከበደል ነጻ የሚሆን ማን ነው?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዳዊት ግን አቢሳን፦ “ልትገድለው አይገባህም! ቀብቶ ያነገሠውን ንጉሥ የሚጐዱ ሰዎችን እግዚአብሔር ራሱ ይቀጣል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጁን የሚ​ዘ​ረጋ ንጹሕ አይ​ሆ​ን​ምና አት​ግ​ደ​ለው” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዳዊትም አቢሳን፦ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን የሚዘረጋ ንጹሕ አይሆንምና አትግደለው አለው።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 26:9
11 Cross References  

ዳዊትም፥ “ታዲያ ጌታ የቀባውን ለማጥፋት እጅህን ስታነሣ እንዴት አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው።


ዳዊትም፥ “ ‘ጌታ የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል የገዛ አፍህ መስክሮብሃልና፥ ደምህ በራስህ ላይ ይሁን” አለው።


ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፥ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ ሳመው፥ እንዲህም አለው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ጌታ ቀብቶህ የለምን?


አቢሳም ዳዊትን፥ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ ላይ ጥሎታል፤ አሁንም እኔ አንድ ጊዜ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋር ላጣብቀው፤ መድገምም አያስፈልገኝም” አለው።


አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህ አድርጌ ከሆነ፥ ዓመፃም በእጄ ቢኖር፥


እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”


ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ፥ “ሺምዒ በጌታ የተቀባውን የረገመ ስለሆነ፥ መሞት አይገባውምን?” አለ።


የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፥ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።


ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements