1 ሳሙኤል 26:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “አንተ ብርቱ ሰው አይደለህምን? በእስራኤልስ ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? እነሆ፤ አንድ ሰው ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር፤ ታዲያ አንተ ንጉሥ ጌታህን ያልጠበቅኸው ስለ ምንድነው? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ዳዊትም ለአበኔር እንዲህ አለ፤ “አንተ ብርቱ ሰው ነህ? በእስራኤልስ ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? እነሆ፤ አንድ ሰው ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር፤ ታዲያ አንተ ንጉሥ ጌታህን ያልጠበቅኸው ስለ ምንድን ነው? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ዳዊትም “አበኔር! አንተ በእስራኤል የታወቅህ ታላቅ ሰው አይደለህምን? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን በደንብ የማትጠብቀው ስለምንድን ነው? እነሆ፥ ከእኛ አንድ ሰው ጌታህን ለመግደል ወደ ሰፈር ገብቶ ነበር፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ዳዊትም አቤኔርን፥ “አንተ ጐልማሳ አይደለህምን? በእስራኤል ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? ጌታህን ንጉሡን ለመግደል አንድ ሰው ገብቶ ነበርና ጌታህን ንጉሡን የማትጠብቅ ስለምን ነው? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ዳዊትም አበኔርን፦ አንተ ጕልማሳ አይደለህምን? በእስራኤል ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? ጌታህን ንጉሡን ለመግደል አንድ ሰው ገብቶ ነበርና ጌታህን ንጉሡን የማትጠብቅ ስለ ምን ነው? See the chapter |