1 ሳሙኤል 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ዳዊትም “እንደተለመደው ሁሉ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ከእኛ ተጠብቀዋል፤ በተራ ተልእኮ ውስጥ እንኳ የሰዎቹ ዕቃዎች የተቀደሱ ናቸው፤ ዛሬማ ምንኛ የበለጠ ቅዱሳን መሆን ይገባቸዋል?” ሲል መለሰ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ዳዊትም “እንደተለመደው ሁሉ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ከእኛ ተጠብቀዋል፤ ባልተቀደሰ ተልእኮ ውስጥ እንኳ የሰዎቹ ዕቃዎች የተቀደሱ ናቸው፤ ታዲያ ዛሬማ እንዴት!” ሲል ለካህኑ መለሰ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ዳዊትም ለካህኑ መልሶ “ከብላቴኖቼ ጋር ወደ ተልእኮ በምሄድበት ጊዜ ሁሉ ከሴቶች እንርቃለን፤ ተራ ተልእኮ እንኳ በምናደርግበት ጊዜ ብላቴኖቼ ንጽሕናቸውን ይጠብቃሉ። ዛሬማ ምንኛ የበለጠ ቅዱሳን መሆን ይገባቸዋል?” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ዳዊትም ለካህኑ መልሶ፥ “ከሴቶች ተለይተን ወደ መንገድ ከወጣን ዛሬ ሦስተኛ ቀናችን ነው። እኔም ብላቴኖቼም ንጹሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰውነቴ ንጽሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መንገድ የነጻች አይደለችም” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ዳዊትም ለካህኑ መልሶ፦ በእውነት ከወጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሦስት ቀን ጠብቀናል፥ የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት፥ ስለዚህ ዛሬ እቃቸው የተቀደሰች በመሆንዋ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል አለው። See the chapter |