Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 2:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ይህ በሁለቱ ልጆችህ በሖፍኒና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 “ ‘በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚደርሰው ላንተ ምልክት ይሆንሃል፣ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 የሁለቱ ልጆችህ የሖፍኒና የፊንሐስ ዕድል ፈንታ ምልክት ይሆንሃል፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ይህ በሁ​ለቱ ልጆ​ችህ በአ​ፍ​ኒ​ንና በፊ​ን​ሐስ ላይ የሚ​መጣ ለአ​ንተ ምል​ክት ነው፤ ሁለቱ በአ​ንድ ቀን በጦር ይሞ​ታሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ይህ በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፥ ሁለቱ በአንድ ቀን ይሞታሉ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 2:34
10 Cross References  

ጌታ ይህን ምልክት ይሰጣል፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱ ላይ ያለውም ዐመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካይነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይህ እንደ ተፈጸመ ወዲያውኑ ትገነዘባለህ’” አለ።


የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ።


ወሬውን ያመጣውም ሰው፥ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሠራዊቱም ከፍተኛ እልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት።


አኪያም የሚናገረውን የትንቢት ቃል በመቀጠል ለኢዮርብዓም ሚስት እንዲህ አላት፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ቤትሽ ተመልሰሽ ሂጂ፤ ወደ ከተማም እንደ ገባሽ ወዲያውኑ ልጁ ይሞታል።


በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።


ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።”


በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በሰዎች ሰይፍ ያልቃሉ።


እነዚህ ምልክቶች በተፈጸሙ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ።


የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከ፥ ዐማቷና ባሏም ስለ ሞቱ፥ “ክብር ከእስራኤል ተለይቷአል” ስትል የሕፃኑን ስም ኢካቦድ አለችው።


ከዚያም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርኳልና ክብር ከእስራኤል ተለይቶአል” አለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements