Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 2:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እነሆ፥ ለቤትህ ሽማግሌ እንዳይገኝ፥ የአንተንም ክንድ፥ የአባትህንም ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እነሆ፤ በዘርህ ሽማግሌ እንዳይገኝ ያንተን ኀይልና የአባትህን ቤተ ሰብ ኀይል የምሰብርበት ጊዜ ይመጣል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እነሆ፥ ከአንተ ቤተሰብ መካከል አንድም ሰው ወደ ሽምግልና ዕድሜ እንዳይደርስ አንተንና የአባቶችህን ቤተሰብ የማጠፋበት ጊዜ እየተቃረበ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እነሆ፥ ዘር​ህ​ንም፥ የአ​ባ​ት​ህ​ንም ቤት ዘር የማ​ጠ​ፋ​በት ዘመን ይመ​ጣል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እነሆ፥ ለቤትህ ሽማግሌ እንዳይገኝ፥ ክንድህን የአባትህንም ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 2:31
11 Cross References  

እስራኤል እኔን ከመከተል ርቀው በተቅበዘበዙ ጊዜ፥ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ የራቁት ሌዋውያን ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ።


የክፉዎች ንድ ትሰበራለችና፥ ጌታ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።


መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃቸዋል፥ የወላጅ አልቦችም ክንዶች ተሰብረዋል።


ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያን የሠራዊቱ አዛዥ፥ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾመ።


ኤፉድ ይለብስ የነበረውም አኪያ በመካከላቸው ነበር። እርሱም በሴሎ የጌታ ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ ነበር። ሕዝቡም ዮናታን አለመኖሩን አላወቁም ነበር።


ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመግጠም ሠራዊታቸውን አሰለፉ፤ ጦርነቱ እንደ ተፋፋመም፥ እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፤ በጦርነቱም ላይ አራት ሺህ ያህል እስራኤላውያን ተገደሉ።


በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements