1 ሳሙኤል 19:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በመጨረሻም፥ እርሱ ራሱ ወደ ራማ ሄደ፤ ከዚያም በሴኩ ወዳለው ትልቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ እንደ ደረሰ፥ “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ሲል ጠየቀ። አንድ ሰውም “በራማ በምትገኘው የራማዋ ናዮት ናቸው” ብሎ ነገረው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 በመጨረሻም፣ እርሱ ራሱ ወደ አርማቴም ሄደ፤ ከዚያም በሤኩ ወዳለው ትልቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ እንደ ደረሰ፣ “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ሲል ጠየቀ። አንድ ሰውም “በአርማቴም በምትገኘው በነዋት ዘራማ ናቸው” ብሎ ነገረው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ከዚህ በኋላ እርሱ ራሱ ወደ ራማ ለመሄድ ተነሣ፤ እዚያም ሴኩ በሚባለው ስፍራ ወደሚገኘው ወደ አንድ ታላቅ የውሃ ጒድጓድ በደረሰ ጊዜ “ሳሙኤልና ዳዊት የሚገኙት የት ነው?” ብሎ ቢጠይቅ፥ በናዮት መኖራቸው ተነገረው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ሳኦልም እጅግ ተቈጣ፤ እርሱም ደግሞ ወደ አርማቴም መጣ፤ በመሴፋም አውድማ ወዳለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድጓድ ደረሰ። “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአውቴዘራማ ናቸው” አሉት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 የሳኦልም ቁጣ ነደደ፥ እርሱም ደግሞ ወደ አርማቴም መጣ፥ በሤኩም ወዳለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድጓድ ደረሰ። ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው? ብሎ ጠየቀ፥ አንድ ሰውም፦ እነሆ፥ በአርማቴም አገር በነዋትዘራማ ናቸው አለው። See the chapter |