Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 19:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስለዚህ ዳዊትን እንዲይዙ ሰዎችን ላከ፤ እነርሱም የነቢያትም ጉባኤ በሳሙኤል መሪነት ትንቢት ሲናገሩ ባዩ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ሰዎች ላይ ወረደ፤ እነርሱም እንደዚሁ ትንቢት ተናገሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ ዳዊትን እንዲይዙ ሰዎችን ላከ፤ ይሁን እንጂ፣ የነቢያትም ጉባኤ በሳሙኤል መሪነት ትንቢት ሲናገሩ ባዩ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ሰዎች ላይ ወረደ፤ እነርሱም እንደዚሁ ትንቢት ተናገሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን የሚይዙ ሰዎች ላከ፤ እነርሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ፥ በሳሙኤል መሪነት የተሰበሰቡ ነቢያት በጉባኤ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ትንቢት ሲናገሩ አዩ፤ በዚህን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ሰዎች ላይ ስለ ወረደ እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ትንቢት ተናገሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ያመ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙ​ኤ​ልም አለ​ቃ​ቸው ሆኖ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሞ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሳ​ኦል መል​እ​ክ​ተ​ኞች ላይ ወረደ፤ እነ​ር​ሱም ትን​ቢት ይና​ገሩ ጀመር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሳኦልም ዳዊትን ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ሰደደ፥ የነቢያት ጉባኤ ትንቢት ሲናገሩ፥ ሳሙኤልም አለቃቸው ሆኖ ሲቆም ባዩ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል መልእክተኞች ላይ ወረደ፥ እነርሱም ትንቢት ይናገሩ ጀምር።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 19:20
13 Cross References  

ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጉሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊይዙት ዘቦችን ላኩ።


ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፥ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ወጣቶቻችሁም ራእይ ያያሉ፥


ጊብዓ በደረሱ ጊዜ፥ እነሆ የነቢያቱ ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ተናገረ።


ሳኦል ዳዊትን እንዲይዙት ሰዎች በላከ ጊዜ ሜልኮል፥ “እርሱ ታሟል” አለቻቸው።


ሳኦልም የዳዊትን ቤት ከበው በማለዳ እንዲገድሉት ሰዎችን ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮል ግን፥ “ሕይወትህን ለማትረፍ በዚህች ሌሊት ካልሸሸህ፥ በነገው ቀን ትገደላለህ” ብላ አስጠነቀቀችው።


ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽ፥ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰው ይናገራል።


በለዓምም ዓይኑን አንሥቶ እስራኤል በየነገዱ ተቀምጦ አየ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ መጣ።


ለሳኦልም፥ “እነሆ፤ ዳዊት ራማ በምትገኘው በናዮት ተቀምጧል” ብለው ነገሩት።


ሳኦልም ይህ በተነገረው ጊዜ ሌሎች ሰዎች ላከ፤ እነርሱም ትንቢት ተናገሩ፤ ሳኦል ለሦስተኛ ጊዜ ሰዎች ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements