1 ሳሙኤል 14:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ “እናንተ በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሰዎቹም፥ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ሳኦልም እስራኤላውያንን ሁሉ፣ “እናንተ በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሰዎቹም፣ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ብለው መለሱለት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 ከዚያም በኋላ ሳኦል “እናንተ ሁላችሁም በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 እስራኤልንም ሁሉ፥ “እናንተ አንድ ወገን ትሆናላችሁ፤ እኔና ልጄ ዮናታንም አንድ ወገን እንሆናለን” አለ። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ደስ የሚያሰኝህን አድርግ” አሉት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 እስራኤልንም ሁሉ፦ እናንተ በአንድ ወገን ሁኑ፥ እኔና ልጄ ዮናታንም በሌላ ወገን እንሆናለን አለ። ሕዝቡም ሳኦልን ደስ የሚያሰኝህን አድርግ አሉት። See the chapter |