1 ሳሙኤል 14:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 በምርኮው ላይ ተረባርበው በጉን፥ በሬውንና ጥጃውን በመውሰድ በመሬት ላይ ዐርደው ሥጋውን ከነደሙ በሉት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 በምርኮው ላይ ተረባርበው በጉን፣ በሬውንና ጥጃውን በመውሰድ በመሬት ላይ ዐርደው ሥጋውን ከነደሙ በሉት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ስለዚህም ከጠላት ባገኙት ምርኮ ላይ እየተረባረቡ በጎችን፥ የቀንድ ከብቶችንና ጥጆችን ባገኙበት ቦታ እያረዱ ሥጋውን ከነደሙ መብላት ጀመሩ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ሕዝቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎችን፥ በሬዎችንም፥ ጥጆችንም ወስደው እንዳገኙ በምድር ላይ አረዱ፤ ሕዝቡም ከደሙ ጋር በሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 ሕዝቡም ለምርኮ ሳሱ፥ በጎችን በሬዎችንም ጥጆችንም ወስደው በምድር ላይ አረዱ፥ ሕዝቡም ከደሙ ጋር በሉ። See the chapter |