Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 12:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከዚያም ጌታ ይሩበኣልን፥ ባርቅን፥ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በሰላም ትኖሩ ዘንድ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ እጅ ታደጋችሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም እግዚአብሔር ይሩባኣልን፣ ባርቅን፣ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ ያለ ሥጋት ትኖሩ ዘንድ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ እጅ ታደጋችሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔርም መጀመሪያ ጌዴዎንን፥ ከዚያም በኋላ ባራቅንና ዮፍታሔን፥ ከዚያም ሶምሶንን፥ በመጨረሻም እኔን ላከ፤ እኛም እያንዳንዳችን እናንተን ከጠላቶቻችሁ አዳናችሁ፤ በሰላምም ኖራችሁ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሩ​በ​ኣ​ልን፥ ባር​ቅ​ንም፥ ዮፍ​ታ​ሔ​ንም፥ ሳሙ​ኤ​ል​ንም ላከ፤ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም ካሉት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ እጅ አዳ​ኑ​አ​ችሁ፤ ተዘ​ል​ላ​ች​ሁም ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔርም ይሩበአልን፥ ባርቅንም፥ ዮፍታሔንም፥ ሳሙኤልንም ላከ፥ በዙሪያችሁም ካሉት ከጠላቶቻችሁ እጅ አዳናችሁ፥ ተዘልላችሁም ተቀመጣችሁ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 12:11
13 Cross References  

ስለዚህም፥ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፥ “ይሩበኣል” ብለው ጠሩት።


ዲቦራ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባራቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺህ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤


በዚህ ጊዜ ጌታ ወደ እርሱ ዘወር ብሎ፥ “ባለህ ኃይል ሂድ፤ እስራኤውያንን ከምድያማውያን እጅ ነጻ እንድታወጣ የምልክህ እኔ አይደለሁምን? አለው”


በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለተመቱ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም። ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ የጌታ እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።


እንዲሁም ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን ያደረገላቸውን በጎ ነገር ሁሉ አስበው ለቤተ ሰቡ ውለታ መላሽ ሆነው አልተገኙም።


የኢዮአስ ልጅ ይሩባኣል ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ በዚያም ተቀመጠ፤


በዚህ ጊዜ ኢዮአስ በቊጣ ለገነፈለውና በዙሪያው ለነበረው ሕዝብ እንዲህ አለ፤ “ለበኣል ትሟገቱለታላችሁን? ልታድኑትስ ትሞክራላችሁን? ለእርሱ የሚሟገትለት ቢኖር እስከ ጠዋት ይሙት! እንግዲህ በኣል በእርግጥ አምላክ ከሆነ መሠዊያውን ሲያፈርሱበት ራሱን ሊከላከል ይችላል።”


ይሩበኣል የተባለው ጌዴዎን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጠዋት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተ ሰሜን በኩል፥ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።


ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል የታመነ የጌታ ነቢይ መሆኑን ዐወቁ።


ስለዚህም እግዚአብሔር እስራኤልን ከሶርያውያን እጅ ነጻ የሚያወጣቸው መሪ ላከላቸው፤ እነርሱም ከዚያ በፊት በነበረው ዓይነት በሰላም ኖሩ።


የኡላምም ልጅ ባዳን ነበረ፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ነበሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements