1 ሳሙኤል 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደ፤ የሳኦልንም ንጉሥነት በጌታ ፊት አጸና። በዚያም ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ፤ ሳኦልና እስራኤላውያንም ሁሉ በታላቅ ደስታ አከበሩት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደ፤ የሳኦልንም ንጉሥነት በእግዚአብሔር ፊት አጸና። በዚያም ሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ፤ ሳኦልና እስራኤላውያንም ሁሉ ታላቅ በዓል አደረጉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልጌላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት የሳኦልን ንጉሥነት አጸደቁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ በዓሉንም ሳኦልና መላው ሕዝብ በታላቅ ደስታ አከበሩት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን ቀብቶ በእግዚአብሔር ፊት በጌልጌላ አነገሠው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የእህል ቍርባንና የሰላም መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፥ በዚያም ሳኦልን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ አነገሡት፥ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ፥ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ። See the chapter |