1 ነገሥት 8:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ‘ስሜ ይጠራበታል’ ወዳልከው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት ይመልከቱ፤ አገልጋይህም በዚህ ስፍራ የምጸልየውን ጸሎት ስማ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ባሪያህ ወደዚህ ቦታ የሚያቀርበውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፣ ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’ ወደ አልኸው በዚህ ስፍራ ወዳለው ቤተ መቅደስ ዐይኖችህ ሌትና ቀን የተከፈቱ ይሁኑ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ስሜ ይጠራበታል ወዳልከው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቀንና ሌሊት ተመልከት፤ እኔም አገልጋይህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ የምጸልየውን ጸሎት ስማ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ሌሊትና ቀን የተገለጡ ይሁኑ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ‘በዚያ ስሜ ይሆናል፤’ ወዳልኸው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ሌሊትና ቀን የተገለጡ ይሁኑ። See the chapter |