Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 7:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 ንጉሥ ሰሎሞን የጌታ ቤት ሁሉንም ሥራ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለጌታ ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፥ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በጌታ ቤት ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሠራው ሥራ ሁሉ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ አባቱ ዳዊት የቀደሰውን ብሩንና ወርቁን፣ ዕቃዎቹንም ሁሉ አምጥቶ በእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አኖራቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፥ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 እንዲሁ ንጉሡ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ ብርና ወርቅ፥ ዕቃም፥ ሰሎሞን አገባ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ በነበሩ ግምጃ ቤቶች አኖረው።

See the chapter Copy




1 ነገሥት 7:51
15 Cross References  

እንዲሁም ሰሎሞን ለጌታ ቤት የሚሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን የብርና የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰሎሞን አምጥቶ በጌታ ቤት ውስጥ በነበረው ግምጃ ቤት አኖረው።


የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ፥ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል፤ የሠራዊት ጌታም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


ይህም ቤት በንጉሡ በዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባል ወር በሦስተኛው ቀን ተፈጸመ።


በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን ተከለ፤ በአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ዘረጋ። በዚህ ዓይነት ሙሴ ሥራውን ፈጸመ።


አባቱ ለጌታ የተለዩ እንዲሆኑ ያደረጋቸውንና እርሱም ራሱ ከወርቅና ከብር አሠርቶ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ ያደረጋቸውን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ በቤተ መቅደስ አኖረ።


በዚህ አኳኋን ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሥራ ፈጸመ፤ ጣራውንም ከውስጥ በኩል ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ አግዳሚ ሠረገላና ጠርብ ለበደው።


በዚህ ዓይነት ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ፈጸመ።


ጽናዎችንና ዱካዎችን ከብርና ከወርቅ የተሠሩ በመሆናቸው ወሰዱአቸው።


እነርሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝገቡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አልተላለፉም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements