Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 7:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ የአሸንድዬ አበባ የሚመስሉ ከነሐስ የተሠሩ ጉልላቶች ነበሩ። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ዓይነት ተፈጸመ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ዐናቱ ላይ ያሉት ጕልላቶች የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበራቸው። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ሁኔታ ተፈጸመ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ የአሸንድዬ አበባ የሚመስሉ ከነሐስ የተሠሩ ጉልላቶች ነበሩ። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ዐይነት ተፈጸመ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በአ​ዕ​ማ​ዱም ራስ ላይ የሱፍ አበባ የሚ​መ​ስል ሥራ አደ​ረገ። እን​ዲ​ሁም የአ​ዕ​ማዱ ሥራ ተጨ​ረሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በአዕማዱም ራስ ላይ የሱፍ አበባ የሚመስል ሥራ ነበር፤ እንዲሁም የአዕማዱ ሥራ ተጨረሰ።

See the chapter Copy




1 ነገሥት 7:22
4 Cross References  

በመመላለሻው ምሰሶዎች አናት ላይ ያሉት ጉልላቶች ቁመታቸው አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ሲሆን የአሸንድዬ አበባን በሚመስል ሥራ ተጊጠው ነበር።


ሑራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምሰሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፤ ከቤተ መቅደሱ መግቢያ በር በስተ ደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሰሶ ደግሞ ቦዔዝ ተባለ።


ሑራም ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ጥልቀት፥ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የክብ ማእከል ርዝመት፤ ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ዙሪያ ያለው አንድ ክብ ገንዳ ከነሐስ ሠራ።


ሁለቱ ምሰሶዎች፥ በምሰሶዎቹም ላይ የነበሩትን ማቶቶች የሚመስሉ ጉልላቶች፥ በምሰሶውም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች የሚሸፍኑት ሁለቱ መረቦች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements