Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 4:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ስለ ሰሎሞን ጥበብ ሰምተው የእርሱን ጥበብ ያዳምጡ ዘንድ መልእክተኞቻቸውን ይልኩ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ጥበቡን ከሰሙት ከዓለም ነገሥታት ሁሉ የተላኩ፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ የሰሎሞንን ጥበብ ለማድመጥ መጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ስለ ሰሎሞን ጥበብ ሰምተው የእርሱን ጥበብ ያዳምጡ ዘንድ መልእክተኞቻቸውን ይልኩ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ፥ ጥበ​ቡን ሰም​ተው ከነ​በሩ ከም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ለመ​ስ​ማት ሰዎች ይመጡ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ከአሕዛብም ሁሉ፥ ጥበቡንም ሰምተው ከነበሩ ከምድር ነገሥታ ሁሉ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ሰዎች ይመጡ ነበር።

See the chapter Copy




1 ነገሥት 4:34
6 Cross References  

የምድርም ነገሥታት ሁሉ ጌታ በልቡ ያኖረውን ጥበብ ለመስማት የሰሎሞንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር።


ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።


የሠራዊት ጌታም እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከሁሉም የአሕዛብ ቋንቋ ዐሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና እኛም ከእናንተ ጋር እንሂድ” ይላሉ።


በዘመኑም ፍጻሜ፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ ከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።


የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቶና ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቁ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ልትፈትነው መጣች፤ ወደ ሰሎሞንም በገባች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው።


ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች በምሳሌ እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements